የአዊ/ብሔ/አስ/ትራ/ሎጄ/ጽ/ቤት

የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች

ከመምጣትዎ በፊት አስበውበት ይምጡ

አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በሙሉ ዝርዝር እዚህ ላይ ያገኛሉ

ማስታወሻ: ሁሉም አገልግሎቶች የሚሰጡት የስራ ሰዓታችን በሚከተለው መልኩ ነው፦ ከሰኞ እስከ አርብ ሰዓት 2:30 ሰዓት እስከ 6:30 እና ከ7:30 እስከ 11:30 ሰዓት
1. ለአዲስ ተሽከርካሪ ሰሌዳና ሊብሬ ለማውጣት
  • የተሟላ የጉምሩክ ዲክለራሲዩን እና ተሽከርካሪውን ማቅረብ
  • የግዥ ደረሰኝ (Invoice)
  • የአስመጭው የንግድ ፈቃድ እና የአምራቹ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ (ሮዝ ወረቀት)
  • የታደሰ መታወቂያ (ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ)
  • 2% የቴብር ቀረጥ መክፈል
2. ለተሽከርካሪ መሰረታዊ ፋይል ዝውውር
  • የግብር ክሊራንስ ለኮድ 1 እና ኮድ 3
  • የወቅቱን ቦሎ ማድረግ
  • የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ መግባትና የመንገድ ፈንድ ማቅረብ
  • የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ)
3. የተሽከርካሪ ግምት ለማስገመት (ስመ-ንብረት) ዝውውር ለማሰራት
  • ከገቢዎች የግብር ክሊራንስ ማቅረብ
  • በፍትህ የፀደቀ የሻጭና የገዥ ውል
  • የወቅቱን ቦሎ ማድረግ
  • ሻጭና ገዥ መታወቂያ ይዞ በአካል መቅረብ/በውክልና ከሆነ ህጋዊ ውክልና
  • በገዥ ስም 2% እና በሻጭ ስም 2% የተከፈለ ደረሰኝ ማቅረብ
4. አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ) ለማስደረግ
  • የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ መግባት
  • የመንገድ ፈንድ መግዛት
  • ከህጋዊ የምርመራ ተቋም የምርመራ ውጤት ማቅረብ
  • ሊብሬ ይዞ መቅረብ
5. የጠፋ ሰሌዳ ወይም ሊብሬ ለመውሰድ
  • የፖሊስ ማስረጃ ማቅረብ
  • ስለመጥፋቱ በአዲስ ዘመን የታወጀ ጋዜጣ ማቅረብ
6. የተሽከርካሪ እገዳ
  • የፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ፣የባንክ/ኢንሹራንስ/የገንዘብ ቁጠባ እና ገቢዎችና ጉምሩክ የማገጃ ደብዳቤ
  • እግዱን ለማሳገድ 1000 ብር መክፈል
7. የተሽከርካሪ እገዳ ማንሳት
  • መጀመሪያ የታገደበትን ቁጥር እና ቀን የያዘ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣የባንክ/ኢንሹራንስ/የገንዘብ ቁጠባ እና ገቢዎችና ጉምሩክ የማስነሻ ደብዳቤ
8. የጥገና ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት/ማደስ
  • የሰው ሀይል መረጃ፣የቢሮ አደረጃጅትና የመሳሪያ አደረጃጅት
  • ለጥገና ተቋሙ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት
9. አዲስ መንጃ ፈቃድ ለመውሰድ
  • የተግባር እና የንድፈ ሃሳብ ፈተና ማለፍ
  • ማሰልጠኛ ተቋሙ የሰጠዎትን ባጅ እና መታዎቂያ ይዞ መቅረብ
  • 1500 ብር ክፍያ በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን አካውንት በባለመንጃፈቃድ ስም ገቢ አድርገው ዋናውን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ
10. መንጃ ፈቃድ ለማደስ
  • የጤና ምርመራ/የሜዲካል/ ውጤት ከመንግስት ወይም ከግል የጤና ተቋም ማቅረብ
  • የሚታደሰውን መንጃ ፈቃድ ማቅረብ
  • ውክልና ከሆነ የፍትህ ውክልና ማቅረብ ለ 2 ጊዜ ብቻ
  • በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን አካውንት በባለመንጃፈቃድ ስም ገቢ ያደረጉበትን የክፍያ ደረሰኝ ማቅረብ

የእድሳት የክፍያ ሁኔታዎች

የዘገየበት ቀን ብዛት ክፍያ ቅጣት ጠቅላላ
የእድሳት ቀን ካለለፈ 1400 ብር የለም 1400 ብር
ከ1-30 ቀናት መዘግየት 1400 ብር 300 ብር 1700 ብር
ከ31-90 ቀናት መዘግየት 1400 ብር 800 ብር 2200 ብር
ከ91-365 ቀናት መዘግየት 1400 ብር 1500 ብር 2900 ብር
ከ365 ቀናት በላይ የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ፈተና ይወስዳሉ
11. የጠፋ መንጃ ፈቃድ መስጠት

አንድ አሽከርካሪ መንጃ ፈቃዱን ከወሰደ በኋላ ሊጠፋበት, ሊሰረቅ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች መንጃ ፈቃዱን ካጣው ስለመጥፋቱ ከ ፖሊስ ሁኔታ የሞላ ስለመሆኑ ማስረጃ ሲያቀርብ እና በቅጣት አለመያዙን ከመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቡድን አረጋግጦ መውሰድ ይችላል:: የጠፋ መንጃ ፈቃድ ለመውሰድ 3000 ብር ቅጣት በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን አካውንት በባለመንጃፈቃድ ስም ገቢ አድርገው ዋናውን ደረሰኝ ማቅረብ::

12. የተጎዳ/የተሰበረ መንጃ ፈቃድ መስጠት

አንድ አሽከርካሪ መንጃ ፈቃዱ ቢሰበርበት ወይም ከላይ ያሉ ጽሁፎች ቢፋቁበት እና ለአጠቃቀም የሚያስቸግር ከሆነ መንጃ ፈቃዱን ድጋሚ መውሰድ ይችላል:: የተጎዳ መንጃ ፈቃድ ድጋሚ ለመውሰድ 1500 ብር በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን አካውንት በባለመንጃፈቃድ ስም ገቢ አድርገው ዋናውን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ብቻ ነው::

13. የመንጃ ፈቃድ ስም ለውጥ

አንድ አሽከርካሪ የመንጃ ፈቃዱን ስም የፍርድ ቤት ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ይዞ በመቅረብ ማስቀየር ይችላል:: የመንጃ ፈቃድ ስም ለመለወጥ 1500 ብር በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን አካውንት በመጀመሪያ ስሙ ገቢ አድርገው ዋናውን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ::

14. የመንጃ ፈቃድ ፋይል ዝውውር

ለመውሰድ:

  • መታዎቂያ
  • መንጃ ፈቃድ
  • በክልል ውስጥ ከሆነ 500 ብር ከክልል ወጪ ከሆነ 700 ብር በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን �አካውንት በባለመንጃፈቃድ ስም ገቢ አድርገው ዋናውን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ
  • እንቀበላለን የሚል ደብዳቤ ፋይሉን ከሚወስድበት ተቋም ማምጣት አለበት

ለማምጣት:

  • በአካል በመቅረብ እንቀበላለን የሚል ደብዳቤ መውሰድ
  • ፋይሉ ካለበት ተቋም ደብዳቤ ይዞ በመሄድ በፖስታ ቤት እንዲላክ ማድረግ አለበት
  • ፋይሉ መድረሱን ካረጋገጡ በኋላ በክልል ወስጥ ከሆን 500 ብር ከክልል ወጪ ከሆነ 2100 ብር በአብክመ ትራ/ሎ/ባለስልጣን አካውንት በባለመንጃፈቃድ ስም ገቢ አድርገው ዋናውን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ
15. መንጃ ፈቃድ ኢንተርናሽናል ማድረግ

አንድ አሽከርካሪ ከኢትዮጵያ ውጪ የመሄድ እድል ቢያጋጥመው መንጃ ፈቃድ በሄደበት አካባቢ እንዲያገለግለው ማስረጃወችን ማለትም የጉዙ ፈቃድ፣ ቪዛ፣ ፓስፖርት፣ የውጭ ሀገር የትምህርት እድል ወረቀት ይዞ ቀርቦ ኢንተርናሽናል ማድረግ ይችላል::

16. ኦፕሬተር ፈቃድ ለማደስ ወይም ለማውጣት
  • ሊብሬ
  • ቦሎ የዘመኑ
  • 3ኛ ወገን
  • በእንጅባራ መናኸሪያ ፀደይ ባንክ አካውንት 1000 ብር ገቢ አድርጎ ደረሰኝ ማቅረብ
  • ለማደስ ነባሩን የኦፕሬተር ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ
  • ተሽከርካሪውን በአካል ማቅረብ
  • ባለንብረቱ/ህጋዊ ተወካይ በአካል ቀርቦ ማመልከት
17. የተሸከርካሪ ድንገተኛ ቴክኒክ ምርመራ
  • ተሸከርካሪዉን በአካል ማቅረብ
  • ቼክሊስቱን ማቅረብ
  • የአገልግሎት ክፍያ ከፍሎ ያስያዙትን መንጃ ፍቃድ መዉሰድ
18. ወደ ሌላ ዞን መሸኛ ለመውሰድ
  • ከማህበሩ ከዕዳ እገዳ ነፃ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ
  • ቀድሞ የፀደቀውን መርሃ ግብር መመለስ
19. ለመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቡድን
  • ከታሪፍ በላይ ካስከፈለዎት፣እቃ ከጠፋብዎት እና እንግልት ወከባ ወይም መዝለፍ ከደረሰብዎ ምስክር በመያዝ ለመን/ትራ/ደህ/ቡድን በጽሁፍ ማመልከት ይችላሉ::/ስልክ ቁጥር 058-227-1000